Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ በሚያስገነባው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመልሶ ማቋቋሚያ ቦታ ላይ ለግንባታ መሳሪያዎች (ድንጋይ መፍጫ፣ ብሎኬት ማምረቻ) የመትከያ ቦታ ዝግጅት እና ተያያዥ ስራዎች ዲዛይን እና ግንባታ (Site Preparation, design & construction of Facilities for Construction Equipment, Rock Crusher and HCB Machines at Bishoftu City-Resettlement site on Turkey basis) ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: - SSNT-T571

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቢሾፍቱ ከተማ በሚያስገነባው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመልሶ ማቋቋሚያ ቦታ ላይ ለግንባታ መሳሪያዎች (ድንጋይ መፍጫ፣ ብሎኬት ማምረቻ) የመትከያ ቦታ ዝግጅት እና ተያያዥ ስራዎች ዲዛይን እና ግንባታ (Site Preparation, design & construction of Facilities for Construction Equipment, Rock Crusher and HCB Machines at Bishoftu City-Resettlement site on Turkey basis) ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በ 120 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኘ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T571 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ለ 150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፈው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቲጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517- 8024

ኢ-ሜይል: KoyachewT@ethiopianairlines.com

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

 

Save Tender