የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች እና የግንባታ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የሚያሟሉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች እና የግንባታ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የሚያሟሉ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. ዕቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የንግድ ፈቃድ ያደሱ፤
2. የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ
3. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ የተደራጁበትን የሥራ ዘርፍ የሚገልጽ እና በ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. Tin Number ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
5. በገንዘብ ጽ/ቤት ለአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /በሲፒኦ/ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከገበያው ዋና በጣም ወርዶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይየሥራ ቀናት ሰነዱን በሐረማያ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመከፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታውን ሰነድ በሚገባ በመሙላት አንድ ኦሪጅናልና፣ ኮፒ ብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በሐረማያ ከ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን 6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሑድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
11. ተጫራቾች በሁሉም የጨረታ ገፅ ላይ መፈረምና ማህተም መምታት ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታውን ሰነድ ገዝቶ የሚሞላው የሚያቀርበው ዕቃ በሃገር አቀፍ ደረጃ ጥራቱ የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0989794555 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሐረማያ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
