በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ከቅደመ መደበኛ - 8ኛ ከፍል የተማሪና የአስተማሪ መጻሐፍት ሕትመት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማሳተም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድርመስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ ።
ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ከቅደመ መደበኛ - 8ኛ ከፍል የተማሪና የአስተማሪ መጻሐፍት ሕትመት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማሳተም ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድርመስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ ።
በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የአቅርቦት የምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ግብር ክሊራንስ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
1. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬከቶሬት ግዥ ቡድን ከፍል በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
2. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 - 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 400,000.00 / አራት መቶ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም ህጋዊ ባንከ ጋራንቲ /unconditional Bank Guarantee/ ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
5. ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ የቴከኒካል ጨረታ ሰነድ ሁለት ኮፒና አንድ ኦርጅናል በማዘጋጀት በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማዘጋጀት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
6. ተጫራቾች የህትመት ማሽነሪን በተመለከተ ህጋዊ ሰነድ አቅርበው በመስክ ምልከታ ወቅት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች ጨረታ በሚያቀርቡበት ወቅት ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ማቅርብ አለባቸው::
8. የጨረታ የማስከበሪያን በተመለከተ በቴከኒካል ሰነድ ውስጥ ማቅርብ አለባቸው፡፡ በፋይናንሺያል ጨረታ ሰነድ ውስጥ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ተደረጎ ያስያዘው ጨረታው ማስከበሪያው ዋስትና ይመለስለታል፡፡
9. ጨረታው ለ3 ወራት / 90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
10. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ግዥ ከፍል ማግኘት ይቻላል፡፡
11.ቢሮው ህትመቱ የስራ ቦታንና የማሽነሪ ሁኔታ በመስክ ምልከታ የማድረግ መብት አለው፡
12. ተጫራቾች መጽሐፍቱን በክልሉ የሚገኙ ወረዳ ት/ጽ/ቤቶች እና ከተማ አስ/ር ት/ጽ/ቤቶች ድረስ አጓጉዘው ማስረከብ አለባቸው፡፡ (የቦታዎቹ ትከከለኛ ርቀትና ስም ዝርዝርበጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸ መሆኑን እንገጻል)
13. የመጽሐፍቱ ጠቅላላ ድምር ዋጋ ላይ የተሰራው የድምር ስህተት ከ2% በመብለጥም ወይም በማነስ ከሆነ ከጨረታ ውድደር ውድቅ ይሆናል፡፡
14.ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጅው ዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ ብቻ የአንድ መጽሐፍ ዋጋን በአጠቃላይ መጽሐፍት ህትመት ብዛት በማስላት በትከከል አጠቃላይ ድምርማስቀመጥ አለባቸው፤
15. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ አድራሻው ከቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን በስተ ጀርባ
ስልክ ቁጥር 046-221-70-02
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ሀዋሳ
