Tender Detail

Tender Details

  • Company Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 439 00 75
  • Website
  • Deadline08 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-08 00:00:00
  • Categories Merchandise , Vehicle Spare Parts

የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የከባድና ቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጀኔራል አይተምስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Emergency Relief Transport Enterprise (ERTE) (የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት)


 

የከባድና ቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጀነራል አይተምስ ግዥ ግልፅ ጨረታ መመሪያ

 

ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የከባድና ቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጀኔራል አይተምስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች በተመለከተ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራቱ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ መቅረብ የሚችል፣
  3. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደርበትን ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አስቀድሞ ድርጅቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተመሠከረ የከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ አድርገው በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሺያል ኦርጅናል፣ ፋይናንሺያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የፋይናንሺያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በዚሁ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ነገር ግን የጨረታ መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ በአምስት ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ/ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና አገልግሎት የሚውል ከአጠቃላዩ የግዢው ዋጋ 10 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል ይፈፅማሉ፡፡
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

የድርጅቱ የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት - 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት - 11፡00 ሰዓት

በስልክ ቁጥር፡- 0114390075/1569/3592/0114391027

ፋክስ፡- 0114-39-63-36 ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው።

 

የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት

 

Save Tender