የሲዳማ ከልል መ/ወንሾ ወረዳ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ቋሚ የኤሌከተሮኒከስ ዕቃ እና ዓላቂ የቢሮ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲ/ብ/ክ/መ/ማዕ/ሲ/ዞን የወንሾ ወረዳ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ከልል መ/ወንሾ ወረዳ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ቋሚ የኤሌከተሮኒከስ ዕቃ እና ዓላቂ የቢሮ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች –
-
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤
-
የ2018 ዓ.ም ግብር የገበሩ፤
-
የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
-
የባንክ CPO 10% ማስያዣ ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች የጥራት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
-
የሽያጭ ዋጋ ላይ 2% ግብር ለመክፈል ፍቃደኛ የሆኑ፤
-
ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
-
በአቅራቢዎች ምዝገባ የተመዘገቡ፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ሲመጡ ዋናውን እና ኮፒ ዶክመንት በአንድነት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በተከታታይ 25 (ሃያ አምስት ) ቀን ጀምሮ በወንሾ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት በመቅረብ ለዚህ አገልግሎት ብቻ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች መወዳደርያ የጨረታ ዝርዝር ሰነድ በወንሾ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ሰነድ ወንሾ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ከቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከወጣበት ከ18/12/17 እስከ 6/01/2018 ዓ/ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በዕለቱ ካልተገኙ ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
በሲ/ብ/ክ/መ/ማዕ/ሲ/ዞን የወንሾ ወረዳ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት
