Tender Detail

Tender Details


አዋሽ ባንከ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበረውን ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)


ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንከ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበረውን 12 ተሽከርካሪዎች በሎት (1) እና በሎት (2) (ጄኔሬተሮች፣ የብር መቁጠሪያ ማሽን፣ መፈተሻ ማሽን፣ የሂሳብ መደመሪያ፣ የዶላር መፈተሻ ማሸን፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ታይፕራይተር፣ የሙቀት መለኪያ፣ የአየርማቀዝቀዣ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ፋከስ፣ የወረፋ መጠባበቂያ፣ ቦይለር፣ ቴሌቪዥን፣ ቴፕ ሪከርደር፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ ኤ ቲ ኤም ሼልተር፣ ዲከሰን ሼልፍ፣ የመጽሐፍ መደርደሪያ፣ ፋይሊንግና ላተራል ፋይሊንግ ካቢኔት፣ ሴኪውሪቲ ፋይሊንግ ካቢኔት፣ የገንዘብ ማስቀመጫ ሣጥን(ካዝና)፣ የኮት መስቀያ፣ መጋረጃ፣ የተለያዩ ባትሪዎች፣ ዩ ፒ ኤስ፣ ስታብላይዘር፣ የስልክ ቀፎ፣ የጄኔሬተር ቤት፣ የጥበቃ ቤት፣ ብረታ ብረቶች፣ ፍራሽ ካውንተርና እምነበረድ፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ የማስታወቂያ ምልከቶችን እና የኔትዎርከ ኬብሎች) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡-

1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ ከኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣

2. እያንዳንዱ ተጫራች (በሎት 1) ላይ ለተገለጹት ተሸከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

3. እያንዳንዱ ተጫራች (በሎት 2) ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ ሄኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንከ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

4. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣

5. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታከስ(VAT) 15%፣ ለተሸከርካሪዎቹ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን ይከፍላል፣

6. ንብረቶቹን አሸዋ ሜዳ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ባንኩ እያስገነባ በሚገኘው ሕንጻ ቅጥር ግቢ በአካል ቀርቦ በጨረታው ሰነድ ላይ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፣

7. ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደርዋና ከፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣

8. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

10. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 0115-303014/0115-303026 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

አዋሽ ባንክ አ.ማ.

 

 

Save Tender