Tender Detail

Tender Details


በምስራቅ ወለጋ ዞን የኢባንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ባለበጀት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅህፈት እና የጽዳት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣ የመኪና ጥገና፣ የግንባታ መሳሪያዎች፣ የእጽዋት ዘር እና የእንስሳት ሕከምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በምስራቅ ወለጋ ዞን የኢባንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ወለጋ ዞን የኢባንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ባለበጀት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅህፈት እና የጽዳት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣ የመኪና ጥገና፣ የግንባታ መሳሪያዎች፣ የእጽዋት ዘር እና የእንስሳት ሕከምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያስባችሁ ማስረጃ፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዱንም በዘመኑ የታደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ወይም TOT ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርTIN ማቅረብ የሚችሉ፤

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ከገቢዎች ባለስልጣን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤

6. ያሸነፉበት ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ኢባንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ከፍል አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ የሚችሉ፤

7. ጥራታቸውን የጠበቁ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚችሉና ጥራት የሌላቸውን ዕቃዎችን መቀየር የሚችሉ፤

8. ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ የተመሰከረለት የከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ በአንዱ ዘርፍ 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችሉ፤ በጥቃቅንና አነስተኛ እንተርፕራይዝ አዋጅ መሰረት የተደራጁ ከሆነ ደግሞ ካደራጀው እካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤

9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከኢባንቱ ` ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ማንኛውም ተጫራች ከመ/ቤቱ የገዛውን የጨረታ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ወይም ቲኦቲ (TOT) ጨምሮ በመሙላት ዶክመንቱን ፈርሞና ማህተም ኣድርጎ ምንም ሳያጓድል ዋናውን እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻም ሁለቱን ፖስታ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀለት የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡

11. የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 1 በግለጽ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም (በሌሉበት ይከፈታል)፡፡

12. ከፍያ የሚፈጸመው የታዘዘውን ዕቃ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ነው፡፡

13. መስሪያ ቤቱ ዕቃዎችን 20% ይጨምራል ወይም ይቀንሳል፡፡

14. መ/ቤቱ ከነቀምቴ ከተማ 138 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 466 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ፡- ኢባንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 09-10-

82-56-36/ 09-17-24-44-48 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡

የኢባንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender