Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል
  • Address ምዕራብ ወለጋ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0930076418
  • Website
  • Deadline10 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityለመድሃኒት የህክምና መሳሪያ እና ህትመት ግዢ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር እና 10,000 (አሥር ሺህ) ብር
  • opening date2025-09-10 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Pharmaceutical Products , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዘመን የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች መድኃኒት እና ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የሚገኘው የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዘመን የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች መድኃኒት እና ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣

1ኛ- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የ 2017 ግብር የከፈሉ፡፡

2ኛ- ተጫራቾቹ በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3ኛ- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የታደሰውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

4ኛ- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠለት ለመድሃኒት የህክምና መሳሪያ እና ህትመት ግዢ (CPO) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ብር እና 10,000 (አሥር ሺህ) ብር ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

5ኛ- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ አለባቸው።

6ኛ- የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ታሽጎ ነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡

7ኛ- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን ነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በመቅረብ በባለሙያ ታይቶ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

8ኛ- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጠር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡

9ኛ- የሚቀርበው ሰነድ ድልዝ ስርዝ መኖር የለበትም ፡፡

10ኛ- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶችን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ከነጆ አጠቃላይሆስፒታል የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ ፡፡

11ኛ, ጨረታው የሚከፈተው ከሃያ የሥራ ቀን በኋላ በማግስቱ በ3:00 ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ውክልና ያላቸው ሰዎች አጠገብ በ4፡00 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።

12ኛ- ተጫራቾች በተጠቀሰው ሰዓት ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡

13ኛ- ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርበው መሣሪያ ብራንድና ማርኩን ግልጽ አድርጎ በሠነድ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡

14ኛ- እንደ አስፈላጊነቱ ከተጫራቾቹ አሸናፊ የሆኑ ጋር የውል ስምምነት እስከ ሰኔ 30/2018 ሊቆይ ይችላል።

15ኛ- በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የጨረታውን ግዴታ ባይወጣ ለውል ማስከበሪያ 10% ያስያዘውን ገንዘብ ለሆስፒታሉ ገቢ ይሆናል፡፡

16ኛ- ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብታችን የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0930076418/093076419 አለላቸው

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ በነጆ ወረዳ የነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል

 

Save Tender