Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline15 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security500,000.00
  • opening date2025-09-15 00:00:00
  • Categories Architectural And Construction Design

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሆሮሬሳ, ሻላ ቢላ ቀበሌ, አርሲ ነገሌ ወረዳ ምዕራብ አርሲ ዞን, ኦሮሚያ ከልል የ kindergarten KG (የህጻናት ትምህርት ቤት) ዲዛይን ክለሳና ግንባታ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-SSNT-T561

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሆሮሬሳ, ሻላ ቢላ ቀበሌ, አርሲ ነገሌ ወረዳ ምዕራብ አርሲ ዞን, ኦሮሚያ ከልል የ kindergarten KG (የህጻናት ትምህርት ቤት) ዲዛይን ክለሳና ግንባታ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል። ድርጅቱ በ 270 ቀናት ውስጥ ሥራውን ሰርተው ማስረከብ ከሚችሉ ድርጅቶች ተዋውሎ ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ኃይል እና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. በዘርፉ ለመስራት ለ2017 ዓ.ም ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው

2. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ 2017 ዓ.ም የታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC/BC-5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያለው።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣

4. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣

5. የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

6. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና በ ኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢ እና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር/አንድ መቶ ብር/በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T561 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ። በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት(ስራ) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንከ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት አሮጊው የሰው ሀብት ህንፃ አጠገብ በሚገኘው የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል

ስልከ ቁጥር 011-517-4552

ወ/ሮ ብርትካን ሰመ

 

ኢ-ሜይል: BirtukanS@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender