የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን ሎት 1፡- ቋሚ ዕቃዎችና፣ ፕሪንተር ሌሎች የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት3፡- ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ሎት4፡- የጽዳት ዕቃዎች ሎት 5:- የሰራተኛ 6 ደንብ ልብስ ሎት6፦ ኮምፒውተርና ፕሪንተር ጥገና ሎት 7- የመስተንግዶ የካፌ እገልግሎት ሎት 8፡- በስብሰባ ወቅት የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 9፡- ህትመት ሎት 10- የመስተንግዶ እገልግሎት ሎት 11- የዲጄ እና ዲኮር አገልግሎት ሎት:- 12 ሎት 13 የሁለት ወር እንቁላል ጣይ ዶሮ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት
የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን ሎት 1፡- ቋሚ ዕቃዎችና፣ ፕሪንተር ሌሎች የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት3፡- ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ሎት4፡- የጽዳት ዕቃዎች ሎት 5:- የሰራተኛ 6 ደንብ ልብስ ሎት6፦ ኮምፒውተርና ፕሪንተር ጥገና ሎት 7- የመስተንግዶ የካፌ እገልግሎት ሎት 8፡- በስብሰባ ወቅት የትራንስፖርት አገልግሎት ሎት 9፡- ህትመት ሎት 10- የመስተንግዶ እገልግሎት ሎት 11- የዲጄ እና ዲኮር አገልግሎት ሎት:- 12 ሎት 13 የሁለት ወር እንቁላል ጣይ ዶሮ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ ቲን ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ፈቃድና የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው። የሰራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ለተደራጁ በተወዳደሩብት ዘርፍ አምራች መሆናቸውን የሚገልጽ እና በጥቃቅን አነስተኛ ተደራጅተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የድጋፍ ደብዳቤ ስታመጡ ደብዳቤው በጽ/ቤቱ ኃላፊ ቲተርና ፊርማ ተፈርሞ ማምጣት ግዴታ ነው። ደብዳቤ መኖር አለበት የቫት ተመዝጋቢ፣ (2% እና 10% የሚፈቀደው ለመስተንግዶ ካፌ አገልግሎት ብቻ ነው።) ፣ቲን ሰርተፍኬት፣ እና የዘመኑን ንግድ ፈቃድና የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው በተጨማሪ የደረጃ ዕድገት ሰርተፍኬት፣ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር እና የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የሙያ ብቃት ሠርተፍኬት እና ከተደራጁበት የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት መቻል አለባቸው የመስተንግዶ የካፌ ቤት ኪራይእና መብራት ውሃ ነጻ ነው።
2. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ በእያንዳንዱ ሎት 300/ ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር /ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ 3ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ግዴታ ማስያዝ አለባቸው።
5. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ወጪ እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች በጨረታው ስፔስፊኬሽን መሰረት ብቻ እና ናሙና መቅረብ ግዴታ ነው።
7. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ላይ 10፡30 ተዘግቶ በማግስቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅና መመሪያ መሰረት በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ።
10. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት 1፡- 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር)፤ ሎት 2፡- 20,000( ሃያ ሺህ)፣ ሎት 3፡- 6000( ስድስት ሺህ) ሎት 4፡-30,000 (ሰላሳ ሺህ) ሎት 5፡-11,500(እስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ) ሎት 6፡- 2000(ሁለት ሺህ) ሎት 7፡- 10,300(አስር ሺህ ሶስት መቶ) ሎት 8፡- 1000(አንድ ሺህ) ሎት 9፡- 3000(ሶስት ሺህ) ሎት 10-5000(አምስት ሺህ) ሎት 11- 5000(አምስት ሺህ) ሎት 12፡- ሎት 13 የሁለት ወር እንቁላል ጣይ ዶሮ ግዥ 5000(አምስት ሺህ)።
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብቻ ሊያሰራ የሚችል ሲያሰራም ለቂ/ክ/ከ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ብሎ ማሰራት ይኖርበታል። (ቼክና ጥሬ ገንዘብ ቢድ ቦንድ ማስያዝ አይቻልም።)
አድራሻችን፡- አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት ከያሬድ ቤተ ክርሰቲያን ከፍ ብሎ መስቀል ፍላወር አጠገብ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ
ስተጨማሪ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 01-18-27-59-18
ማሳሰቢያ ለሰራተኛ ካፌ አገልግሎት አስተዳደሩ የውሀ የመብራት እና የኪራይ አገልግሎት ከፍያ እራሱ ይሸፍናል።
የቂርቆስ ክፍስ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት
