Tender Detail

Tender Details


የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለጹትን ለክረምት ለፋብሪካችን ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Metehara Sugar Factory (መተሐራ ስኳር ፋብሪካ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር MSF/LP/05/2025

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለጹትን ለክረምት ለፋብሪካችን ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ጥቅል እንድ፡- የአገዳ ጋሪ ሰንሰለት (chain) ናሙና ያስፈልጋል

ጥቅል ሁለት፡- የከባድ ማሸነሪ መለዋወጫ (power plus, Grade & other spare)

ጥቅል ሶስት ፡- የከባድ ማሽነሪ መለዋወጫ (Grab loader, Volvo spare)

ጥቅል አራት ፡- የዩርሰስ ትራከተር መለዋወጫ

ጥቅል አምስት - የቨርሳታይል ትራከተር መለዋወጫ

ጥቅል ስድስት፡ - ሲቪል ወርክ መለዋወጫ ዕቃዎች (ሚስማር ቆርቆሮና ሌሎች)

ጥቅል ሰባት :- Wooden Pole (አጣና)

ጥቅል ስምንት፦ Bearing (ቤሪንግ) ናሙና ያስፈልጋል

ጥቅል ዘጠኝ ፡- የኤሌከትሪከ መለዋወጫ ዕቃዎች

ጥቅል አስር፡ - Bearing & Electrode (ናሙና ያስፈልጋል)

ጥቅል አስራ አንድ፡- የፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃዎች (Gasket maker, loctite wire brush & other)

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜከሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንገድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ1.5 - 2% የሚሆን በሲ.ፒ.አ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 19 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

7. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0115-505607, 0115-505633 ሜክሲኮ አደባባይ ፊሲፕስ ሕንፃ

አዲስ አበባ

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ

Save Tender