Tender Detail

Tender Details

  • Company በየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ኮተቤ ደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስተጀርባ በኩል 300 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 645 61 99
  • Website
  • Deadline01 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityበየሎቱ የተለያየ
  • opening date2025-09-01 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Maintenance And Repair , Office Supplies And Services , Cloth And Shoes

በየካ ከ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


የእቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ከ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 ደንብ ልብሶች

ሎት ሁለት ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት ሦስት ልዩ ልዩ አላቂ የትምህርት እቃዎች

ሎት አራት ልዩ ልዩ አላቂ የጽዳት እቃዎች

ሎት አምስት ልዩ ልዩ የተገጣጣሚና የጥገና እቃዎች እና

ሎት ስድስት ልዩ ልዩ የቢሮ ቋሚ እቃዎች

በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ከ1-10 ያሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባና የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቫት ተመዝጋቢና ካሽ ሪጅስተር ያለው፣ ታከስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ /በመከፈል ከት/ቤቱ ግዥ ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ለጨረታ ማስረከቢያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ/CPO/ ከሎት እንድ እስከ ሎት አራት ለእያንዳንዳቸው ብር 2000.00/ሁለት ሺህ/ ፤ለሎት አምስት ብር 5000/አምስት ሺ፣ ለሎት ስድስት 10,000 (አስር ሺ) ብር ከጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡

4. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በታሸገ ፖስታ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናልና ኮፒ እሽግ ለይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡

5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒአ ማስያዝ አለበት፡፡

6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ/በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ሳጥኑ ታሽጎ ፣ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው ይከፈታል፡፡

7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንጂ በሌላ ዋጋ ላይተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡

9. ተጫራቶች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ባሉት ሥራ ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት እታ በየአይነቱ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻችን፡- ኮተቤ ደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስተጀርባ በኩል 300 ሜትር ገባ ብሎ ሲሆን ለበለጠ መረጃ ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ስልክ ቁጥር 011 645 61 39

በየካ ክ/ከተማ የደጀዝማች ወንድይራድ አጠቃሳደ ሁስተኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender