Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 002/2017

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት-

በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 002/17 በ15/12/2017 የተለያዩ አልባሳት ፖሊስተር ጨርቅ ጨምሮ፣ ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች የዕይታ መሣሪያዎች (መነጽሮች)፣ የመሬት ምንጣፎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1. በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብርየከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፣

2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው::

3. በሐራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመከፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፣ ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ውድእነኖ ግቢ ነው::

5. ለሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡

6.ተጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጫረት ዕቃዎች ለመግዛት ለሚያቀርበው ዋጋ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበር (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፣

7. በሐራጅ ጨረታ ለመጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባንክ (ንግድ ባንከ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል፡፡

8. የሐራጅ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በዕለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል፣

 

9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋርየሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤

10. እሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የተወዳደሩበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡

11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጹት ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፣

12. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬደዋ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender