Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ጫማ ፤ ያገለገለ ብረታ ብረት belt and radiator እና የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች በግልጽ እንዲሁም ተሽከርካሪ፣ አልባሳት እና ፕሎፕ ጠጠር በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የተጫራቾች ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር -04/2018 ዓ.ም

በጉምሩከ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ጫማ ፤ ያገለገለ ብረታ ብረት belt and radiator እና የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎች በግልጽ እንዲሁም ተሽከርካሪ፣ አልባሳት እና ፕሎፕ ጠጠር በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን

መስፈርቶቹ፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋርተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስከር ወረቀት (ከሊራንስ) እና የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሽከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም ዕድሜው ከ-18-ዓመት በላይ የሆነ የነዥነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።

2. የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺ በታች የሆነ ማንኛውም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ እያስፈልገውም።

3. በተጠቀሰው መስፈርት በጨረታ የሚሸጠው እታ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት ነባረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ስው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይቻልም፡፡

4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅዕ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው ዓምድ ሥር የሚዝዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፈደል ገልጸው እና በተራ ቁጥር 1 ላይየተገለፁትን በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩከ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።

6. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩከ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልጽ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ-05-ተከታታይ የሥ PNG ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመከፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተ በተሰጠው ማስከበሪያ ገሪያ ዋስትና (CPO) የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዘት የጨረታ ማ ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡

8. ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡

9. ተጫራቶች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጧት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

10.ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ እምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ የተረጋገጠ ጨረታ እቃዎች መቶ ሺህ ብር (100,000) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

11. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሰው መጠየቅ ይችሳሱ፡፡

 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender