Tender Detail

Tender Details


የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዎች ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1= ኤሌክትሮኒከስ ልታ ግዥ፣ ሎት 2= እስቴሽነሪ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ግዥ ሎት 3= ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ፣ ሎት 4= የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5= ሞተር ላይከል ግዥ፣ እና ሎት 6= የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዎች ባለሥልጣን


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዎች ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ሎት 1= ኤሌክትሮኒከስ ልታ ግዥ፣ ሎት 2= እስቴሽነሪ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ግዥ  ሎት 3= ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ፣ ሎት 4= የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5= ሞተር ላይከል ግዥ፣ እና ሎት 6= የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት በጨረታው እንዲሳተፍ እየጋበዝን በጨረታው ላይ ለመካፈል አቅራቢው ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት አለበት፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፣

2. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/ አስራአምስት/ ተከታታይየሥራ ቀናት ከፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

3. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመለከት የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው ከቢሮ ቁጥር 06 በ200 መቶ ብር በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለውድድር ሲቀርቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1= 50,000, ሎት 2= 20,000, ሎት 3= 35,000, ሎት 4 = 5,000, ሎት 5= 40,000, እና ሎት 6= 50,000 በባንክበተመሰከረ CPO በፖስታ አሸገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታ ማስከበሪያ ቼከ ተቀባይነት የለውም፡፡

5. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በዓል ወይም የእረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቶች የፋይናንሻልና የቴከኒክ መገምገሚያ መስፈርት በመሙላትና በተለያየ ሁለት

ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንስና የቴከኒክ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ የፋይናንስ 2ኮፒ እና የቴከኒክ 2ኮፒ ፖስታ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡

7. ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስ ማካተት አለማካተቱን በፋይናንሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልጽ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም የተሰጠው ዋጋ ስለግብርምንም የማያወራ ከሆነ የሰጡት ዋጋ ግብርን ያካተተ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡

8.ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይችልም፡፡

 

9. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በጽሑፍ ከተግለጸለት በኋላ በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ CPO በመያዝ ከመ/ቤቱ ጋርውል መፈራረም አለበት፡፡

10. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅትን ወከሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ቀርቶ ተወካይ ከሆነ ሕጋዊ ውክልና ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡

11. ለጨረታው ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፈው ተጫራች ግዴታውን በውሉ መሠረት ካልፈጸሙ በውሉ ላይ በሚገለጸው ሕግ መሠረት መ/ቤቱ ተፈፃሚ የማድረግ መብት አለው፡፡

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት የእያንዳንዱ ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት በፋይናንሻል በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም /መሙያ/ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፡፡

13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ሀዋሳ የዱሮ ደህዱን ጀርባ እንገኛስን፡፡

ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0462125156 ይደውሱ፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዎች ባስሥልጣን

 

Save Tender