Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115584896
  • Websitehttps://tsedeybank-sc.com/
  • Deadline28 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-08-28 00:00:00
  • Categories Education And Training , Business, Industry And Factory Foreclosure , System Supply And Installation

ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)


ፀደይ ባንክ /አ.ማ/ Tsedey Bank (S.C)

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0020/2017

 

ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Lot 1 – Supply, Installation, Configuration, Training and Support of Smart POS Device

የዕቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታው መዝጊያ ቀን

የጨረታው መክፈቻ ቀን

POS Device

pcs

200

ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00

ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30

 

Lot 2 – Vulnerability Assessment & Penetration Testing Solution Acquisition

የዕቃው አይነት

የጨረታው መዝጊያ ቀን

የጨረታው መክፈቻ ቀን

Vulnerability Assessment & Penetration Testing Solution

ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00

ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00

 

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት /ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

  1. የ2017 ዓ.ም የታደስ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው ይገባል። ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከነሐሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ውል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  5. የጨረታው መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ አበባ ለገሃር ስልክ ቁጥር 0911089281/0911383713

 

ፀደይ ባንክ አ.ማ

 

Save Tender