በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሳይትና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
የመጀመሪያ ዙር የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሳይትና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርት
- በጨረታው ለመሳተፍ በመስኩ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
- ዋጋ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻሉን አንድ እና ኦርጅናል አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን በትክክል ማስፈር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ተሽከርካሪዎች ውስጥ ቢያንስ በቁጥር አንድ የኪራይ ተሽከርካሪ የግል ንብረት መሆኑን ሊብሬ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ተሽከርካሪዎች ወጪ በራስ ይሸፍኑና ድርጅቱን የሚጠይቁ ይሆናል፣
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፣
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው የሚሰረዝ ሆኖ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣቸው የአገልግሎት እና እቃ የግዥ ጨረታዎች ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፣
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፋይናንስና ሎጂስቲክስ ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ፣
- የጨረታ ጊዜው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (15) አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፤
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ (15) አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በአስራ አምስተኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ 9:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ይታሽግና በ9:30 ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ30ቀናት ፀንቶ ይቆያል፣
- ተጫራቾች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ ባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ከሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- በጨረታው የቀረቡ የአገልግሎት ግዥ ሆነ የዕቃ ቁጥሩን እንደ አስፈላጊነቱ መ/ቤቱ ሲጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ 0467751979/0916853591 /0930755002
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
