በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ያላቸው የእንስሳት መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ያላቸው የእንስሳት መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚወዳደሩ አቅራቢ ድርጅቶችን ይጋብዛል፡፡ በመሆኑም፡-
- በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፊኬት ያላቸው
- የዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ያላቸው እና መድኃኒቱን ሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርቡ፣ ሌሞ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን 6000 /ስድስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸውና የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጅናል ከላይ የተገለጸውን ማስረጃዎች ጭምር በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁ.14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
ጨረታውም በ15ኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ከቀኑ 8፡30 ላይ የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሲቢያ፡- የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በዕለቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉለውም፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በማ/ኢ/ክ/መንግስት በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
