Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline01 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-01 00:00:00
  • Categories Agricultural

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ በሥሩ ለሚያስተዳድረው የላይ ብር እርሻ ልማት ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር


የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር EAC 004/2018

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ በሥሩ ለሚያስተዳድረው የላይ ብር እርሻ ልማት ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚያቀርቡ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ የሚያቀርቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

2. የሚገዙትን ዕቃዎችን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ) ብቻ በመከፈል ጉርድ ሾላ ላሜ ዴይሪ ግቢ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ለአስራ አምስት ቀናት አየርላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ከጥዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በታሸገ ፖስታ በዋናው መስሪያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ጨምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 108 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ብሔራዊ በዓል/የእረፍት ቀን/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

7.ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0116733497/0902716793

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር

Save Tender