Tender Detail

Tender Details

  • Company ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር
  • Address ሜክሲኮ ,ሠንጋተራ የነጋዴዎች ሕንፃ 23ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115571399
  • Websitehttps://shegersacco.com/
  • Deadline20 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2% (ሁለት በመቶ)
  • opening date2025-08-21 00:00:00
  • Categories Consultancy Service , Business, Industry And Factory Foreclosure , Research Consultant

የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር የማማከር አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን/የአማካሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ ሙያዊ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር


 

የአማካሪ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 የተቋቋመበትን ዓላማ በተሻለ ሁኔታ ለመፈፀም በቀጣይም ይበልጥ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የተቋሙ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ፣ ዝርዝር መዋቅራዊ አደረጃጀት/የማህበሩን የሰው ሀብት አደረጃጀት፣ የሰራተኞች የሥራ መዝርዝር፣ ተፈላጊ ችሎታ፤ የደመወዝና ጥቅማጥቅም እና የሰራተኞች የምደባ መመሪያ ለማሰራት የማማከር አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን/የአማካሪ ድርጅቶችን አወዳድሮ ሙያዊ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

ፍላጎት ያላችሁ አማካሪ ድርጅቶች ዝርዝር መነሻ ሀሳብ (Detailed proposal) ከሚከተሉት ህጋዊ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

  1. ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ (Technical proposal)
  2. የማማከር አገልግሎት ሥራዎቹ ዝርዝር የፋይናንስ መነሻ ሀሳብ (Financial proposal)
  3. በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርትፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የግብር ከፋይነት ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችል፣ ወይም የህብረት ሥራ ማህበራትን የማማከር የአገልግሎት ሰጪነት ህጋዊ ፈቃድ ከህብረት ሥራ ኤጀንሲ ያለው ድርጅት መሆን አለባቸው።
  • የጨረታ ሂደቱ የማህበሩን የግዥ ሂደት የተከተለና በሀገሪቱ የግዥ ህግ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ ህንፃ 23 ፎቅ ዘወትር በቢሮ በስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋውን 2 በመቶ በሲፒኦ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል (ፖስታ) ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ ሰነዳቸውን ለየብቻ በመሙላት ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ማሰ/ህብረት ሥራ ማህበር በሚል በተቋሙ አድራሻ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ለተጫራቾች ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ (Technical proposal) የሚሆናቸውን ዝርዝር ቢጋር (TOR) የያዘ ሰነድ በማህበሩ የፋይናንስ እና ግዥ ክፍል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት የሚቆይ/ከሰኞ እስከ አርብ ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና ቅዳሜ ጧት ከ2፡30 እስከ 6፡30/ ሆኖ ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል መነሻ ሀሳብ ሰነዳቸውን ካስገቡ በኋላ በእለቱ 10ኛዉ ቀን ከሰአት በኋላ 11:30 ላይ ተዘግቶ በማግስቱ ማለትም በ11ኛዉ የሥራ ቀን ላይ ጧት በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
  6. የጨረታው መክፈቻ 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት በማህበሩ ዋና ቢሮ የሚከፈት ይሆናል።
  7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስለ ጨረታው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ቀጥሎ ባለው የስልክ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ስልክ 0115571399 ወይም 0948051115 ወይም 0911997050

 

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/መ/የህብረት ሥራ ማህበር አዲስ አበባ

 

Save Tender