አምቦ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ዩንዬን በዩንዬናችና ሕብረት ሥራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብአት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
አምቦ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ዩንዬን በዩንዬናችና ሕብረት ሥራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብአት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም፡-
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፈቃድ፣ ግብር ስለመክፈሉ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለምን አገልግሎት እንደሚጠቀሙበት የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንደማያቀርቡ ለአምቦ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5% CPO በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አምቦ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ስም ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፤ የጨረታው ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ሲመለስ፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች በዩንዬኑ መጋዘን በአካል በመገኘት ለምርት ግብአት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ያለበትን ሁኔታ በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 500 ለእያንዳንዱ ለምርት ግብአት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ከዩንዬኑ በመግዛት የሚገዙበትን የአንድ ኩንታል ዋጋ በብር መስጠት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡05 ሰዓት ጠዋት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- የተጫራቾች የማስጫኛ ዋጋ ራሳቸው የሚችሉ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ለምርት ግብአት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ በዩንዬኑ መጋዘን ውስጥ ተሰብስቦ የሚገኘውን በመለየት ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የሚረከብ ይሆናል።
- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎችን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተም፣ ስም እና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ በጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ 0112609101፣ 0112363399 ይጠቀሙ
የአምቦ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒዬን ኃላ/የተ/
