Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
  • Address ባህርዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-222-11-00
  • Website
  • Deadline23 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security1%
  • opening date2025-08-23 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Maintenance And Repair , Mechanical Work and Materials

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና ሥራ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ዓመታዊ ውል መፈፀም ይፈልጋል።

Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር አ.ገ.መ.ኮ.ኤ 02/2018

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና ሥራ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ ዓመታዊ ውል መፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እና 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና ሥራ የአገልግሎት ግዥ የሥራ ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ በጨረታ መመሪያው ተካቷል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአገልግሎቶች ግዥ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት አገልግሎት ግዥ ጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮንስትራክሽን ኤጀንሲው ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ማስያዝ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ደ/ የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ከ02/12/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 17/12/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግንባታ ግብዓት አቅርቦት ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 17/12/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግንባታ ግብዓት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-222-11-07/0583205551 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፖስታ ሳጥን ቁጥር 382

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

 

Save Tender