Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ቂልጦ ከተማ ስልጤ ዞን : ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 21 33 86 96
  • Website
  • Deadline30 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security40,000
  • opening date2025-08-30 00:00:00
  • Categories Vehicle Spare Parts

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መሥሪያ ቤቶች የሚውል የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መሥሪያ ቤቶች የሚውል የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፡- ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለእቃዎቹ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችህ፡፡

በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ /CPO/ 40,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  8. ጨረታው በ21ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
  9. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው።
  10. ተጫራቾች በሚፈልጉት ዕቃ ላይ መወዳደር ይችላሉ ሆኖም ለአንድ እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 21 33 86 96/09 33 62 02 20

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

ቂልጦ

 

Save Tender