Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address ሞያሌ : ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0464441415
  • Website
  • Deadline15 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security5%
  • opening date2025-08-15 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Spare Parts , Electronics Materials , Cloth And Shoes

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሣሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቶችን አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር 05/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሣሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቶችን አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስከር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00-12:00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በጽ/ቤታችን የዕለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ _ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛ ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡

6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠ በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት) ተዝግቶ 4፡00 ሰዓት (አራት ሰዓት) ላይ ይክፈታል።

7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይሰዓት ይሆናል፡፡

8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሽናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

9. አሽናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-4–44-14-15 ደውሰው መጠየቅ ይችላሉ።

Save Tender