በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በባቢሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የኮሪደር ፖል መብራት መስመሮችን ዝርጋታ ፕሮጀክት ላይ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በባቢሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የኮሪደር ፖል መብራት መስመሮችን ዝርጋታ ፕሮጀክት ላይ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ለእጩዎች መስፈርቶች
- የመብራት ፖል ሙሉ ዝርጋታ መስመሮችን ለመዘርጋት እና ለመስራት የታደሰ የ2018 የአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ግንባታ የስራ ፍቃድ ያለው መሆን አለበት።
- ሶስተኛ ደረጃ የግንባታ ፈቃድ ያለው እና >3 ከዛ በላይ
- የአቅርቦት ማረጋገጫ፡- ከ BMO ወይም ከፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የታደሰ የ2018 ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- ማንኛውም እጩ ከገቢዎች ባለስልጣን VAT እና TIN No ሰርተፊከት ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- ከኦሮሚያ ወይም ከፌዴራል ገቢዎች ባለስልጣን የ2017 የታከስ ከፍያ ግብር መፈጸሙን ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- ኮንተራክተሩ የኮሪደር መብራት ፖል ሙሉ ዝርጋታ መስመሮችን በመዘርጋት እና በመስራት 2 (ሁለት) አመት ወይም ከዚያ በላይ ልምድ ያለው መሆን አለበት፡፡
- በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብቻ ) ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- የመንግስት ግዥ ቅጣቶች- ተጫራቹ ከዚህ ቀደም በመንግስት ግዥ ያልታገዱ ወይም ያልተከለከሉ ለመሆኑ በፌዴራል ወይም BMO ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በሚቀርብ ማስረጃ ወይም በድህረ ገጽ የሚታይ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 5000 (አምስት ሺህ ብቻ) በመከፈል የጨረታ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ከባቢሌ ገንዘብ ቢሮ የግዥ ሂደት መምሪያ መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዶች የቴከኒክ መስፈርቶች እና የጨረታ ዋጋ አንድ ኮፒ እና ኦሪጅናል በተለየ ፖስታ መቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚቀርበው ሰነድ ስርዝና እና ድልዝ ከሆነ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሣጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም። ለበለጠ መረጃ እባከዎን በስልክ ቁጥር 0921845053 /0922903950/0979979730/ በስራ ሰዓት ይደውሉ።
የባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
