አጠና ተራ የሚገኘው የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር የገበያ ማዕከሉን ባለ 7 ወለል ህንጻ የውስጥ ሽንሸና፣ ዕድሳትና ግንባታ ጠቅላላ ኮንትራክተር ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑትን በጨረታ አወዳድሮ በተፈቀደው ፕላን መሰረት ማሰራት ይፈልጋል።
የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር
የገበያ ማዕከል ህንጻ የውስጥ ሽንሸና፣ እድሳትና የግንባታ ስራ ጨረታ
አጠና ተራ የሚገኘው የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር የገበያ ማዕከሉን ባለ 7 ወለል ህንጻ የውስጥ ሽንሸና፣ ዕድሳትና ግንባታ ጠቅላላ ኮንትራክተር ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑትን በጨረታ አወዳድሮ በተፈቀደው ፕላን መሰረት ማሰራት ይፈልጋል።
ለማሻሻያና ግንባታ ስራ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን አክሲዮን ማህበሩ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አሸናፊው ኮንትራክተር ደግሞ የስራ መሳሪያ አቅርቦ የሚሰራበትን የጉልበት ዋጋ ብቻ የሚያቀርብ ይሆናል።
ስለሆነም:-
- ተጫራቾች በዚህ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይ ምዝገባና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- በተመሳሳይ ስራ 5 ዓመት ልምድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 500,00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአ/ማህበሩ ጽ/ቤት መውሰድ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና የብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሲፒኦ አሰርተው ከጨረታው ሰነድና ከስራ ዋጋ መግለጫ ጋር በፓስታ አሽገው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስካለው 10ኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን፣ ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይሆናል።
- የተጫራቾች ምርጫ የሚፈፀመው በ2 ደረጃዎች፣ ማለትም በቴክኒካልና በፋይናሻል ፕሮፓዛሎች ሲሆን፣ ሁለቱም ለየብቻቸው በ 2ኮፒ ፣ አንዱ ኦሪጅናል፣ አንዱ ደግሞ የኦሪጅናል ኮፒ መሆን አለበት። ፋይናንሻል ፕሮፓዛላቸው ውድድር ተሳታፊ የሚሆኑት በቴክኒካል ፕሮፓዛላቸው ያለፉ ብቻ ይሆናሉ።
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ የሚቆየው ለ 60 ቀን ይሆናል።
- አክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- +251-9-85-96-17-37
የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር
