Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ከጦር ኃይሎች ወደ ኮልፌ በሚወስደው መንገድ ከሆላንድ ኤምባሲ ከፍ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913346653
  • Website
  • Deadline14 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price150.00
  • Bid Security8000
  • opening date2025-08-14 00:00:00
  • Categories Finishing Work

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድነት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለመስሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 01 (አንድ) የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ቀለም ማስቀባት ይፈልጋል፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድነት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለመስሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 01 (አንድ) የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ቀለም ማስቀባት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

              1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በመስኩ የተሰመሩበት ሕጋዊ የታደለ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
              2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ቫት ተመዝጋቢ እና የቲን መለያ ቁጥር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
              3. ተጫራቾች የተደራጁ ጥቃቅንና እነስተኛ ከሆነ ካደራጃቸው አካል ወቅታዊና ህጋዊ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም በቅድሚያ ማፃፍ አለባቸው። እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም በትክከለኛ አድራሻ ከሚመለከታቸው አካላት ማፃፍ አለባቸው።
              4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 መሠረተ ዕድጉት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በአካል በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
              5. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዋጋ ከነቫቱ በመግለፅ ፈርማና ማህተም እና አድራሻቸውን በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ዋናውን እና ኮፒውን በ2 ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ የጨረታ ሰነዱን በመሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በግዥ ቢሮ በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
              6. ጨረታው ጋዜጣ ላይ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት መሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ለዓት ይከፈታል።
              7. አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት በአካል ቀርቦ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታው ያለያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
              8. በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይኖርበታል።
              9. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
              10.  የጨረታ መዝጊያ ዕለትና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርቡ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
              11.  ለጨረታ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለሎት-1 8000 /ስምንት ሺ ብር/ CPO በኮ/ቀ/ክ ከተማ በመሰረተ ዕድግት ቅ/እ/ አ/መ/ደ/ት/ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
              12.  ለጥቃቅንና አነስተኞች የግዥ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል።

 

አድራሻ:- ከጦር ኃይሎች ወደ ኮልፌ በሚወስደው መንገድ ከሆላንድ ኤምባሲ ከፍ ብሎ

ስልክ ቁጥር:- 0913346653/0921313443

 

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሠረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender