ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Berhan Insurance S.C (ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ)
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. BERHAN INSURANCE s.c
የህንጻ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም መስፈርቱን የምታሟሉ ህንጻ ያላችሁና መሸጥ የምትፈልጉ ህጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ያላችሁ የህንጻ ባለይዞታዎች ከዚህ በታች በተገለጸው ዝርዝር መስፈርት መሰረት እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
|
ተ.ቁ |
ዝርዝር መግለጫ |
ተፈላጊ መስፈርት |
|
1 |
ጠቅላላ የቦታው ስፋት |
ከ 600 ካሬ ሜትር ያላነሰ |
|
2 |
ህንጻው ያረፈበት |
ከ 500 ካሬ ሜትር ያላነሰ |
|
3 |
የህንጻው ወለል |
ከ G+7 ያላነሰ፤ ምድር ቤት (Basement) ያለው ቢሆን ይመረጣል |
|
4 |
የመኪና ማቆሚያ |
ከ 20 መኪና በላይ ማቆሚያ ቦታ ያለው |
|
5 |
ህንፃው የሚፈለግበት አካባቢ |
ስቴዲየም - እስጢፋኖስ - ኡራኤል - ሃያ ሁለት ስቴዲየም - ኡራኤል - አትላስ - ቦሌ ስቴዲየም - ካዛንቺስ - ኡራኤል - ሃያ ሁለት ስታዲየም - ብሄራዊ ትያትር - ሰንጋተራ - ተ/ሃይማኖት ስታዲየም - ፒያሳ - አራት ኪሎ ስታዲየም - ፍላሚንጎ - ኦሎምፒያ - ቦሌ ስታዲየም - ሜክሲኮ - ቄራ - ጎፋ ስታዲየም - ሜክሲኮ - ልደታ ስታዲየም - ወሎሰፈር - ወንጌላዊት - ሳርቤት ስታዲየም - ጎተራ - መስቀል ፍላወር - ኦሎምፒያ |
|
6 |
የባለቤትነት ማረጋገጫ |
የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና በቀላሉ ሥም ማዛወር የሚቻልና ምንም ዓይነት የሕግ ክርክር የሌለበት |
|
7 |
ተፈላጊ ዶክመንት |
የተሟላ የባለቤትነት ካርታና የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል |
|
8 |
ህንጻው የሚገኝበት ልዩ ቦታ |
ከዋና አስፖልት ፊት ለፊት ወይም ከ100 ሜትር በላይ ገባ ያላለ |
|
9 |
ህንጻው ያለበት ቦታ |
ህንጻው የስትራክቸር፤ የጣራ፤ የወለል ንጣፍ እና ሌሎች ጉድለቶች የሌሉት |
|
10 |
ከንግድ ደንበኖች ጋር |
የተሻለ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት አካባቢ ተመራጭ ይሆናል |
|
11 |
የአሳንሰርና የአደጋ ጊዜ መውጫ |
ህንጻው ቢያንስ አንድ ሊፍትና አደጋ ጊዜ መውጫ ደረጃዎች ያሉት |
|
12 |
የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት |
ዋናው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር በሚቋረጥበት ወቅት ተለዋጭ በቂ ኃይል ያለው ጀነሬተር ያለው ቢሆን ይመረጣል |
|
13 |
የውሃ አቅርቦት |
በህንጻው ምድርና ጣራ ላይ በቂ የውሃ ማጠራቀሚያ ያለው ቢሆን ይመረጣል |
|
14 |
የእሣት አደጋ መከላከያ |
ተንቀሳቃሽ የእሣት ማጥፊያና ህንጻው ላይ የተገጠመ በውሃ የሚሠራ የእሣት ማጥፊያ (Fire hydrant) ያለው ቢሆን ይመረጣል |
|
15 |
የኮሙኒኬሽን አገልግሎት |
የስልክ፤ የኢንተርኔትና የዳታ መስመር ዝርጋታ ያለው |
|
16 |
የሳኒተሪ አገልግሎት |
በያንዳንዱ ህንጻ ወለል በቂ የሆነ የመጸዳጃ ክፍሎችና የእጅ መታጠቢያ ያሉት |
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ወሎ ሰፈር አደባባይ አጠገብ በሚገኘው ጋራድ ሕንጻ ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተጠቀሰው አድራሻ የጨረታ ማስገቢያ የተዘጋጀውን ሠነድ ከሰኞ 28/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰው ሃብትና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 7 የመጫረቻ ሠነዱን በብር 230 (ሁለት መቶ ሰላሳ) ተ.እ.ታ ጨምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀውን የቴክኒካል ቅጽ እንዲሁም ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ተሟልቶ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይሮርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት መገኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ብርሃን ኢንሹራንስ አ.ማ.
ዋናው መስሪ ቤት
ቦሌ መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባዩ ጎን ላይ
ጋራድ ሲቲ ሴንተር 7ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-67-44-23/46/011470-40-54 መደወል ይችላሉ።
