የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊቤ 3ኛ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 7.6 ኪ.ሜ ከዋናው መንገድ ወደ ግድብ፣ ወደ ስዊች ያርድ፣ ወደ ኃይል ማመንጫ እና የመኖሪያ ካምፕ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በኮንክሪት ንጣፍ የማሻሻል የመንገድ ሥራ ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/01/2018
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጊቤ 3ኛ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ 7.6 ኪ.ሜ ከዋናው መንገድ ወደ ግድብ፣ ወደ ስዊች ያርድ፣ ወደ ኃይል ማመንጫ እና የመኖሪያ ካምፕ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በኮንክሪት ንጣፍ የማሻሻል የመንገድ ሥራ ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ እና ሎጅስቲክስ ሕንፃ ምድር ቤት ጀነሬሽን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን የኮንክሪት መዳረሻ የመንገድ ሥራ ግዥ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/01/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 800,000.00 (ስምንት መቶ ሺህ) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ምድር ቤት ጀነሬሽን ግዥ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 57 95 42 መደወል ይችላሉ ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
