የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢንፍላይት ኬተሪንግ (In-flight catering) ማስፋፊያ እና አድሳት ፕሮጀክት ዲዛይን ግምገማ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ ደረጃ የህንጻ ስራ የሀገር ውስጥ ንግድ ፈቃድ ያላቸው አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T550
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢንፍላይት ኬተሪንግ (In-flight catering) ማስፋፊያ እና አድሳት ፕሮጀክት ዲዛይን ግምገማ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ ደረጃ የህንጻ ስራ የሀገር ውስጥ ንግድ ፈቃድ ያላቸው አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ አማካሪዎችን ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለነባር የኢንፍላይት ኬተሪንግ (In-flight catering) አጠቃላይ ማሻሻያ 150 ተከታታይ ቀናት እና ለአዲሱ B+G+3 ህንፃ ሥራው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ (ለዲዛይን ግምገማ 60 የቀን መቁጠሪያ ቀናትን ጨምሮ) 300 ተከታታይ ቀናት ነው።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 23, 2017 ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ እየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T550 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የነቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ እየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ነሐሴ 23, 2017 ዓ.ም ከቀኑ 09፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን 9:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ: - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ - ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ፕሮኪውርመንት እና ሰኘላይ ቼይን ማኔጁመንት- ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-89-18
ኢ-ሜይል: EskedarG@ethiopianairlines.com ወይም ESAYASTS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
