Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline01 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security500,000.00
  • opening date2025-09-01 00:00:00
  • Categories Architectural And Construction Design , Building Construction , Construction Works

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የዋና መስሪያ ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገድ እድሳት፣ የጥገና ክፍል ግቢ በር ማሻሻያ እና የፍተሻ አካባቢ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዲዛይን እና ግንባታ (Bid for Design- Build of ETG Compound Road Renovation and MRO Gate Upgrading & Screening Area Expansion Project on turn-key basis at Addis Ababa Bole International Airport) ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ/ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T552

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የዋና መስሪያ ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገድ እድሳት፣ የጥገና ክፍል ግቢ በር ማሻሻያ እና የፍተሻ አካባቢ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዲዛይን እና ግንባታ (Bid for Design- Build of ETG Compound Road Renovation and MRO Gate Upgrading & Screening Area Expansion Project on turn-key basis at Addis Ababa Bole International Airport) ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ/ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC-¬ ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T552 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ነሐሴ 26, 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩኘ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517- 49-18

ኢ-ሜይል: Ashebir Te@ethiopianairlines.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender