የኦሮሚያ ማይኒንግ ግሩፕ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ስራ የሚውሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ 4 (አራት) ትናንሽና (አንድ) መካከለኛ መኪናዎች ብቃት ያላቸውና በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ኪራይ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የኦሮሚያ ማይኒንግ ግሩፕ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
የኦሮሚያ ማይኒንግ ግሩፕ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ስራ የሚውሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ 4 (አራት) ትናንሽና (አንድ) መካከለኛ መኪናዎች ብቃት ያላቸውና በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ኪራይ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፤
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር) ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ 100 ብር (መቶ ብር) በመክፈል ኦሮሚያ ማይኒንግ ግሩፕ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ህብረት ባንክ አጠገብ ቢፍቱ አዱኛ 8ኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ኦሮሚያ ማይኒንግ ግሩፕ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ቢፍቱ አዱኛ 8ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት ታሽጓ በማግስቱ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የታሸገው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን የመኪና አይነት ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን መኪና በራሳቸው ወጭ ተከራይ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው መኪና አስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- የመኪና ብዛት፤ ሞዴል፤ የተሰራበት ዘመን፤ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚከራይ፤ በአጠቃላይ የኪራይ ውል በሚዘጋጀው የጨረታው ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
አድራሻ፡ ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት ህብረት ባንክ ጎን ቢፍቱ አዱኛ 8ኛ ፎቅ ላይ ነወ።
ስልክ ቁጥር፤ 0115578055/0986120494 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ማይኒንግ ግሩፕ
