በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ) ከጨረታ መመሪያው ጋር የተያያዙትን የሚወገዱ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አዴስፋ/ግጨ/007/2017
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ) ከጨረታ መመሪያው ጋር የተያያዙትን የሚወገዱ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ አካላትና ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀናት ድረስ አዲስ አበባ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርበው ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር (Tin No) ያላቸው በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት መ/ቤት ግዢ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ ድርጅቶች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መሠረት እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሁለት የታሸገ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሆኖ መቅረብ ያለበት ሲሆን በቴክኒካል ፖስታ አስፈላጊ ኦሪጅናል ሰነዶች እና የጨረታ ማስከበሪያ አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች (አቅራቢዎች) ከዚህ በላይ የተገለጹትን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ አዲስ አበባ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ 0910147760/0912102754 በመደወል ወይም ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል፡፡
- ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ
