የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017/18 በጀት ዓመት የኮርፖሬሽኑ ሎጎ የታተመበት ልዩ ልዩ የስጦታ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት እና ሳምፕል መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Agricultural Businesses Corporation (የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ልዩ ልዩ የስጦታ ዕቃዎችን ለማሳተም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/02/2017
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ2017/18 በጀት ዓመት የኮርፖሬሽኑ ሎጎ የታተመበት ልዩ ልዩ የስጦታ ዕቃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መስፈርት እና ሳምፕል መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ፤ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ ፋፋ ፋብሪካ አጠገብ የቀድሞው እርሻ መሣሪያዎችና ቴክኒክ አገልግሎት አ.ማ ግቢ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 110 ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው ነሀሴ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ሆኖ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ በ8፡30 ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ 0114709095/0114-423608
ፋክስ 0114-421312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
