በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የኢንዱስትሪውን ዋና ቢሮ ህንፃ እድሳት ስራ ለማሰራት በስራ ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ቁጥር ቢሞቬኢኢ/ግጨሰ/05/2017
በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የኢንዱስትሪውን ዋና ቢሮ ህንፃ እድሳት ስራ ለማሰራት በስራ ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ (VAT) የተመዘገቡና (Tin No.) ያላቸው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሎቱ በቀረቡት ስራዎች ላይ ለመወዳደር በዘርፉ ስራ ወይም ንግድ ላይ ስለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከዚህ ውጪ ተወዳድረው ቢገኙ ያስገቡት መወዳደሪያና ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 470,000.00 (አራት መቶ ሰባ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖሪባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያውን ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፤ ለወደፊትም በኢንዱስትሪው ጨረታ አይሳተፉም፤ ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር መስራት አለባቸው። በዋጋው ላይ ማንኛውም ታክስና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ መግለፅ ያለበት ሲሆን ምንም ካልተባለ ዋጋው ከነቫቱ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት እንዲኖረው ተደርጎ በነጠላ ዋጋው ተመስርቶ ጠቅላላ ዋጋው ይታረማል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው አንደኛው ቅጅ ላይ “ዋና” በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት ማድረግ ይኖርባቸዋል። በሁለቱ መካከል ያለመጣጣም ቢፈጠር “ዋና” ተብሎ ምልክት የተደረገበት ተቀባይነት ይኖረዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ከዚህ በላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግንባር ቀርበው ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት አለባቸው።
- ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የስራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ተቋም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
- ኢንዱስትሪው ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ዋስትና (Performance Bond) ወይም የባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኋላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በቢሾፍቱ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በቢሾፍቱ ሞተር ቬሂክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ (ልዩ ቦታ 40ሺ) ማግኘት ይችላሉ።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ ቁጥር (09 94 52 15 56 /09 36 65 65 77) ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
- ኢንዱስትሪው ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤
የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ
