የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ እና ለዚሁም ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማሰያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ) በቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- አሸናፊ ድርጅት /ተጫራቹ/ ያሸንፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽህፈት ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ ሲሆን በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከዚሁ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የተፈላጊውን እቃ ጥራት እና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- በሽያጭ ያቀረበውን እቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው አሸናፊ ድርጅቱ /በራሱ ወጪ እቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
- የዕቃውን ማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጐ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽህፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻችን ቡርታ ዲንቱ ገንዘብ ጽ/ቤት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911982478/0967857864/0913119344
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን የቡርቃ ዲንቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
