Tender Detail

Tender Details


ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንሰሳት መድኃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2017

 

ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንሰሳት መድኃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No/ ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
  2. መድሃኒቶቹን በአንድ ጊዜ በአይነት፣ በመጠን በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችል።
  3. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውንና አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 60,000 /ስልሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንከ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት ወይም ገንዘብ ጽ/ቤት በመሂ1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦሪጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት። የዕቃ ግዥ መ/ቤቱን፣ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከሰአት 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በዚሁ እለት /በ16ኛው ቀን ከሰአት 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
  6. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል።
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በተናጠል ነው።
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
  9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን መድሃኒት እና ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ወ/ንብረት ክፍል ድረስ በመውሰድ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
  10. የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚታሸግበት ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  11. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦሪጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል።
  12. ማንኛውም የመድኃኒት አይነት የአገልግሎት ጊዜው 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደ/ብርሃን መስመር ላይ ነው።
  15. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0116 320 147 ወይም 0116 320 745 ደውለው ይጠይቁ።

 

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender