የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ በኤሊዳር ወረዳ የሚገኘውን የሱልጣን አሊሚራ እንግዳ ማረፊያ ማስጠገን ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ በኤሊዳር ወረዳ የሚገኘውን የሱልጣን አሊሚራ እንግዳ ማረፊያ ማስጠገን ስለፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
- አጠቃላይ ስራዎቹ የሚጠናቀቁበት ቀን 270 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ይሆናል።
- ጨረታው የሚካሄደው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህዝባዊ አዋጅ በተዘጋጀ ክፍት ሀገር አቀፍ የጨረታ አሰራር እና ለሁሉም ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ቱሪዝም ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ከጠዋቱ 1፡30–6፡00 እና ከሰአት 9፡00 -11፡30 ድረስ ማየት ይችላሉ።
- የመመዘኛ መስፈርቱ የ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው የምድብ BC/GC-5 እና ከዚያ በላይ፤ ንግድ ፈቃድ፣ ታክስ ክሊራንስ፣ ቫት፣ ንግድ ምዝገባ እና ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በፅሑፍ አቅርበው የማይመለስ ብር 200.00 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሁለት ኤንቨሎፕ በማድረግ የመጀመሪያ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና የጨረታ ማስከበሪያ እና ሁለተኛው የፋይናንሻል ፕሮፖዛል በሚል የተለጠፈ ኤንቨሎፕ በተናጠል በታሸገ እና ሁለቱን ፖስታዎች በሌላ የውጭ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ግምግማ የሚያካሂደው በሁለት ደረጃዎች ሲሆን በመጀመሪያ ደረጃ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ይገመገማል፤ ግምገማ ውጤቱ ከ70% በላይ ያመጡ ተጫራቾች የፋይናንሻል ፕሮፖዛል ይታያል። የሚሰጠው ነጥብም ቴክኒካል 70% ሲሆን ፋይናንሻል ደግሞ 30% ነው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ቀናት ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው ከወጣበት 22ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን በዛው ቀን 9፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ከታች በተጠቀሰው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ ማስያዝ አለባቸው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻችን ሰመራ ከተማ ትራፊክ መብራት አደባባይ አካባቢ ሎማ ህንፃ ፊት ለፊት የሚገኝ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0336660488 ወይም በአካል በመቅረብ ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል።
የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ
