ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ የሚውል ገረጋንቲ ለማምረት እና የቋጥኝ ዲንጋይ ለመሰባበር የሚውል ጃካመር ያለው ኤክስካቫተር ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሆለታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመንገድ የሚውል ገረጋንቲ ለማምረት እና የቋጥኝ ዲንጋይ ለመሰባበር የሚውል ጃካመር ያለው ኤክስካቫተር ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የያዘና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤
- ማሽነሪው የሚከራይበት 300 ሰዓት ሲሆን የማምረቻ ቦታው ሆለታ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ በቢርቢርሰ ሲባ ቀበሌ ውስጥ ነው፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ /በቼክ ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10/100 በባንክ ማስያዝ የሚችል፤
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ የማሽኑን ፣ ነዳጅ ፤ ሎቤድ ማስጫኛውን በራሱ ወጪ እስከ ሆለታ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ በቢርቢርሰ ሲባ ቀበሌ ውስጥ ማቅረብ አለበት፤
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ ሲሆን በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚሁ ቀን 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 1000 ብር ከሆለታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0112370095/0911045695/0922203464 ደውለው መጠየቅ ትችላላችሁ።
የሆለታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
