በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪ በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪ እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪ በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅና በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ስነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በመሆኑም:-
- በመንገድ ግንባታ ማሽነሪ ሐራጅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ፣ የኮንስትራክሽን፣ የማሽነሪ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ በተጨማሪም በተ.ቁ 2 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
- በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
- ተጫራቾች የመንገድ ግንባታ ማሽነሪ እና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሐሙስ ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
- በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የመንገድ ግንባታ ማሽነሪ ሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ ለማሽነሪ ብር 100,000.00 እና የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት። ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰነ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የዕቃ ሐራጅ |
እስከ 21/11/2017 |
22/11/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
|
የዕቃ ግልጽ |
እስከ 22/11/2017 |
23/11/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
||
|
የመንገድ ግንባታ ማሽነሪ ሐራጅ ጨረታ |
እስከ 23/11/2017 |
24/11/2017 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። |
- የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ- 011-470-85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሠልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ሕንፃ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
