በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Ammonium Nitrate, Gelatin /Dynamic, Delay Electric Detonator and Detonatin Cord በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ/56/2016
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ለሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል Ammonium Nitrate, Gelatin /Dynamic, Delay Electric Detonator and Detonatin Cord በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ (የ2017 ዓ.ም)፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የተጠየቁትን ማስረጃዎች ከፒ በመያዝ የማይመለስ ብር 115.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዢ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከቴክኒከ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዢ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በዕለቱ ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዢ መምሪያ ይከፈታል።
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 0114420216 ፋክስ 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
