ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው የቡና ልማቶች አገልግሎት የሚውሉ Mesh Wire and Black shade net በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
ግልጽ የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር EAC 001/2018
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማ በሥሩ ለሚያስተዳድራቸው የቡና ልማቶች አገልግሎት የሚውሉ Mesh Wire and Black shade net በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚያቀርቡ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ የሚያቀርቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
- የሚገዙት ዕቃዎችን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ጉርድ ሾላ ላሜ ዴይሪ ግቢ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በታሸገ ፖስታ በዋናው መስሪያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ድረስ እስከ 5ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 108 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። 5ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116733497/0902716793
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
