የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት የመንገድ መብራት ደረሰኝ ህትመት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሰሜን ሽዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት የመንገድ መብራት ደረሰኝ ህትመት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሱ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር መለያ ቁጥር (Tin no) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ መቶ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 - 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሞ/ወ/ወ/ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በወጣበት በ15 ኛው ቀን ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ይዘጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በሞ/ወ/ወ/በሰላድንጋይ ከተማ መሪ ማ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0116250497 /0921127777 / በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ይህ ማስታወቂያ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና በዕለቱ ቀን የሚውል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወይራ ወረዳ የሰላድንጋይ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት
