የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር የገበያ ማዕከሉን ባለ 7 ወለል ህንጻ የውስጥ ሽንሻኖ ፣ ዕድሳትና ግንባታ ጠቅላላ ኮንትራክተር ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑትን በጨረታ አወዳድሮ በተፈቀደው ፕላን መሰረት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር
የገበያ ማዕከል ህንጻ የውስጥ ሽንሻኖ፣ እድሳትና የግንባታ ስራ ጨረታ
የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር የገበያ ማዕከሉን ባለ 7 ወለል ህንጻ የውስጥ ሽንሻኖ ፣ ዕድሳትና ግንባታ ጠቅላላ ኮንትራክተር ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑትን በጨረታ አወዳድሮ በተፈቀደው ፕላን መሰረት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዚህ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የግብር ከፋይ ምዝገባና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
- በተመሳሳይ ስራ 5 ዓመት ልምድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአ/ማህበሩ ጽ/ቤት መውሰድ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና የብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሲፒኦ አሰርተው ከጨረታው ሰነድና ከስራ ዋጋ መግለጫ ጋር በፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስካለው 10ኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን፣ ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች ምርጫ የሚፈፀሙ በ2 ደረጃዎች፣ ማለትም በቴክኒካልና በፋይናንሻል ፕሮፖዛሎች ሲሆን፣ ሁለቱም ለየብቻቸው በ 2ኮፒ ፣ አንዱ ኦርጅናል፣ አንዱ ደግሞ የኦርጅናል ኮፒ መሆን አለበት። ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ውድድር ተሳታፊ የሚሆኑት በቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ያለፉ ብቻ ይሆናሉ፡፡
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ የሚቆየው ለ 60 ቀን ይሆናል።
- አከሲዮን ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ 251 985 9617 37
የብርሀን ጮራ ኮልፌ የገበያ አዳራሽ አ/ማህበር
