ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሚገኝበት ዋና መስሪያ ቤት የሆኑትን ማለትም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘውን የሕንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የእድሳት ሥራ ለማከናወን ተፈልጓል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/01/2018
ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሚገኝበት ዋና መስሪያ ቤት የሆኑትን ማለትም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘውን የሕንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የእድሳት ሥራ ለማከናወን ተፈልጓል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
ሎት 1፡- የህንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የዲዛይን እና ማማከር ስራ ማከናወን የሚችሉ የኢንቴሪየር ዲዛይን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 011-156 9992
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር
