ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 1 ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GWWC-1/GC-1) የሆኑ የሀገር ውስጥ እና የሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ /Airside/ የውሃ መገኛ ልማት እና የላንድ-ስኬፒንግ ፕሮጀክት ስራን በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design & Construction Turn Key Basis) ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 1 ጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GWWC-1/GC-1) የሆኑ የሀገር ውስጥ እና የሀገር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ /Airside/ የውሃ መገኛ ልማት እና የላንድ-ስኬፒንግ ፕሮጀክት ስራን በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design & Construction Turn Key Basis) ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-
- የፕሮጀክቱ ዲዛይን እና ግንባታ ሥራው 90 ቀናት የንድፍ /Design ዝግጅት ቀናትን ጨምሮ በ420 ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።
- ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ለ2017 ዓ.ም የታደሰ በጠቅላላ የውሃ ሥራዎች ተቋራጭ ደረጃ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 1 (GWWC-1/GC-1) የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T548 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Ship Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ነሐሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፡-
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ +25 11 1517-8918
ኢ-ሜይል: ESAYASTS@ethiopianairines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
