Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
  • Address Bole Road, behind Dembel City Center, Seid Yassin Building., addis ababa,Ethiopia, Phone: 011-1-569992
  • Websitehttps://commercialnominees.com/
  • Deadline28 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50000.00
  • opening date2025-07-28 00:00:00
  • Categories Construction Works

ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሚገኝበት ዋና መስሪያ ቤት ማለትም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘውን የሕንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የእድሳት ሥራ ለማከናወን ተፈልጓል፡፡

Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር CN/NCB/01/2018

 

ድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር የሚገኝበት ዋና መስሪያ ቤት ማለትም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የሚገኘውን የሕንጻው የዋና ስራ አስፈጻሚ ክፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የእድሳት ሥራ ለማከናወን ተፈልጓል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

ሎት 1፡- የዋና ስራ አስፈጻሚ ከፍል እና የስብሰባ አዳራሽ የእድሳት ስራ ማከናወን የሚችሉ ከደረጃ 9 በላይ የግንባታ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡30-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር፡- 011-1-569992

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማኅበር

 

Save Tender