Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline30 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security25000.00
  • opening date2025-07-30 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በመራሮ፣ በቆጂ፣ ሰጉሬ፣ መተሃራ፣ ወለንጪቲ፣ ሲሬ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የሽያጭ ማዕከላት እድሳት እና የአጥር መልሶ ግንባታ ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡበ ምስራቅ ሪጅን በመራሮ፣ በቆጂ፣ ሰጉሬ፣ መተሃራ፣ ወለንጪቲ፣ ሲሬ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የሽያጭ ማዕከላት እድሳት እና የአጥር መልሶ ግንባታ ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የጨረታ መለያ ቁጥር RFQ:-4276571፣ 4276572፣ 4276573፣ 4276578፣ 4276574፣ 4276582 እና 4276581 በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፈቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት ዓመት የስራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መስፈርት

  1. ጨረታው ከሀምሌ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 25,000.00 /ሀያ አምስት ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንከ ሲ.ፒ.አ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ኢትዮ ቴሌኮም

ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

 

Save Tender