ድርጅታችን ብሩከ ኢትዮጵያ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
The Brooke Hospital for Animals. (ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ)
የሞተር ሳይክል ግዢ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር B-ETH/06/2025
ዘብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በቁጥር፡- 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግስት እንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል፡፡
ድርጅታችን ብሩከ ኢትዮጵያ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም ብቁ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1. |
Motor bikes 150cc (BOXER) with full accessories. . capacity 144.08cc . Power 8.83@7500 . Engine 4 stroke |
ቁጥር |
16 |
|
2. |
Helmet |
ቁጥር |
16 |
|
3. |
Carry Box |
ቁጥር |
16 |
- ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሰውን እቃ የማቅረብ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2% ቦንድ በሲፒኦ መልክ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲፒአው የጨረታ ኤንቨሎፕ ውስጥ ለብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሰም የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ከታች በተጠቀሰው የብሩክ ፅ/ቤት አድራሻ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ነው፡፡ የጨረታ ማቅረቢያው (15) አስራ አምስተኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን (በተ.ቁ.3 የተመለከተው) ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-661-0069/011-662-18-85 በመደወል ወይም በኢሜይል info@thebrookeethiopia.org አድራሻችንን መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን፡- 22 ማዞሪያ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ከድልድዩ አጠገብ ነው፡፡
ስልክ 011-661-0069/011-662-1885
ዘብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ
