አምቦ የ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን የኦሮሚያ ሕብርት ሥራ ዩንዬን በዩንዬኖችና ሕብረት ስራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ አፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
አምቦ የ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን የኦሮሚያ ሕብርት ሥራ ዩንዬን በዩንዬኖችና ሕብረት ስራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ አፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶቹም፡-
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፊቃድ፣ ግብር ስለመክፈል የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለምን አገልግሎት እደሚጠቀሙበት የሚያሳይ የድጋፍ ደብዳቤ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዕት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንደማያቀርቡ አምቦ የገበሪዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5%- CPO በኦሮሚያ ሕብርት ሥራ ባንክ አምቦ የገበሪዎች ሕብርት ሥራ ዩንዬን ስም ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፤ የጨረታው ማስከበረያ ለተሸናፊዎች ወድያውኑ ሲመለስ፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በዩንዬኑ መጋዘን በአካል በመገኘት ለምርት ግብዕት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ያለበትን ሁኔታ በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 500 ለእያንዳንዱ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ከዩንዬኑ በመግዛት የሚገዙበትን የአንድ ኩንታል ዋጋ በብር መስጠት አለባችው፤
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውከልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ፊት ወይም ባይገኙትም ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡05 ሰዓት ጠዋት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 16ኛቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- ተጫራቾች የማስጫኛ ዋጋ ለራሳቸው የሚቺሉ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ዩንዬኑ መጋዘን ውስጥ ተሰብስቦ የሚገኘውን በመለየት ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የሚረከብ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎችን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተም ፣ስም እና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡ ዩኒዬኑ በጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0112609101፣ 0112363399ይጠቀሙ
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
